የጦና ንቦቹ ሁለቱን ተስፈኞች ወደ ዋናው ቡድን አሳድገዋል

የጦና ንቦቹ ሁለቱን ተስፈኞች ወደ ዋናው ቡድን አሳድገዋል

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ታዳጊ ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን በማሳደግ የሚታወቁት ወላይታ ድቻዎች ሁለቱን ተስፈኛ ተጫዋቾችን ማሳደግ ችለዋል።

ለሀገር ውስጥ እና ለሀጉራዊ ውድድር ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዳማ ከተማ በማድረግ ላይ የሚገኙት ወላይታ ድቻዎች ሁለት የወደ ፊት ተስፈኛ የሆኑ ተከላካይ ኦፌሶን ኪዳኔ እና የመስመር አጥቂውን አቤኔዜር አለማየሁን ወደ ዋናው ቡድን ማሳደጋቸው ታውቋል። ሁለቱም በወላይታ ድቻ ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ ቡድን ዘንድሮ ተጫውተው ያሳለፉ ሲሆን በROAD TO 2029 National Camping ከተመረጡ ተጫዋቾች መካከል ይገኙበታል።

በተጨማሪም በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተቀላቅለው ከቡድኑ ጋር ልምድ እንዲያገኙ ከተመረጡ ሰባት ተጫዋቾች መካከል የሚገኙ ሲሆን ለሳምንት ከቡድኑ ጋር አብረው ሲሰሩ መቆየታቸውም ይታወቃል።

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራም ሁለቱን ተጫዋቾች በቀጥታ ወደ ዋናው ቡድን እንዳሳደጓቸው ሲታወቅ በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በነበረው የልምምድ ጨዋታ ሁለቱም ተጫዋቾች ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን ለጦና ንቦች ከተቆጠሩ ሁለት ጎሎች አንዱን ኤፌሶን ኪዳኔ ማስቆጠሩ ይታወቃል።