መቐለ 70 እንደርታ የመስመር ተጫዋቹን ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል።
መቐለ 70 እንደርታ የመስመር ተጫዋቹ አሸናፊ ሀፍቱን ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለማቆየት ከስምምነት ደርሰዋል። ከመቐለ ሁለተኛ ቡድን ተገኝቶ ላለፉት ዓመታት ቡድኑን በማገልገል ላይ የቆየው እና በ2011 ከአሳዳጊ ክለቡ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያሳካው ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ23 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1352′ ደቂቃዎች ክለቡን ያገለገለ ሲሆን በውድድር ዓመቱን ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።
በ2015 ዓ.ም ለስድስት ወራት ከተጫወተበት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ የእግር ኳስ ሂወቱ በመቐለ 70 እንደርታ ያሳለፈው አሸናፊ አሁን ደግሞ በክለቡ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል።