በዐፄዎቹ ቤት የነበረውን ቆይታ ያገባደደው ጌታነህ ከበደ ቀጣይ ማረፊያው የት ሊሆን እንደሚችል ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡
በኢትዮጵያ እግርኳስ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ አጥቂዎች መካከል አንዱ የሆነው ጌታነህ ከበደ ከፋሲል ከነማ ጋር የነበረው ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣይ ማረፊያው የት ይሆናል የሚለው ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ቢነሳም የአጥቂው ማረፊያ የብዙ ጊዜ ፈላጊው በመሆን የሚቀርበው ኢትዮጵያ ቡና ሊያስፈርመው እንደሚችል ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቿ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡
የቀድሞው የደቡብ ፓሊስ ፣ ደደቢት፣ የደቡብ አፍሪካው ክለብ ቢድ ዌስት ክለብ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ከደቡብ አፍሪካ ዳግም በመመለስ ደደቢትን በድጋሚ ተቀላቅሎ ከተጫወተ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ወልቂጤ ከተማ ካሳለፈ በኋላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በዐፄዎቹ ቤት ቆይታ ማድረጉ ይታወቃል። አሁን መዳረሻው ቡናማዎቹ ቤት ሊሆን እንደሚችል እና ዝውውሩ ነገ አልያም ማክሰኞ ሊጠናቀቅ እንደሚችል አውቀናል።