ምዓም አናብስት የወጣቱን ተከላካይ ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።
በዘንድሮ የውድድር ዓመት በጥሩ ብቃት በወጥነት ክለባቸውን ካገለገሉ ወጣት ተከላካዮች መሀል አንዱ የሆነው ዘርኢሰናይ ብርሀነ በአሳዳጊ ክለቡ መቐለ 70 እንደርታን ለመቆየት ውሉን ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል።
በ2016 ዓ.ም በትግራይ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዘጋጅነት በተካሄደው ክልል አቀፍ ሊግ ከተሳተፈ በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለመጀመርያ ጊዜ በፕሪምየር ሊጉ የተሳተፈው ወጣቱ ተከላካይ በውድድር ዓመቱ በሀያ አምስት ጨዋታዎች ተሳትፎ 2002′ ደቂቃዎች አሳዳጊ ቡድኑን ያገለገለ ሲሆን አሁን ደግሞ ከእናት ክለቡ ጋር ለተጨማሪ አንድ ዓመት ውሉን ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል። ተጫዋቹ ከኬኔዲ ገብረፃድቕ እና አሸናፊ ሀፍቱ በመቀጠልም ውሉን ለማራዘም የተስማማ ተጫዋች ሆኗል።