በአሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ የሚመሩት ኢትዮጵያ መድኖች ጋናዊ አማካይ ለማስፈረም ተስማምተዋል
ለሚጠብቃቸው የአፍሪካ ቻምፕዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ቻምፕዮኖቹ መድኖች ቀደም ብለው ጋናዊውን ኢስማዒል አብዱልጋኒዩ ለመፈረም መስማማታቸውን መግለፃችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ቆይታ የነበረው ሌላው ጋናዊ አማካይ ማይክል ኦቶሉን ለማስፈረም ተስማምተዋል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ22 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1818′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ይህ ጋናዊ ከዚህ ቀደም በግሬት ኦሎምፒክስ፣ ለፓርቹጋል አምርቶ ፓርቲሞኔንሴ እንዲሁም ለሌጎን ሲቲ መጫወቱ ይታወሳል።