ላለፉት ዓመታት በስዊድኑ ጁርጋርደን ቆይታ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ይስሀቅ ሙሉጌታ ወደ ኢንግሊዙ ኪው ፒ አር አምርቷል።
ከኢትዮጵያዊው አባቱ እና ከኤልሳልቫዶራዊት እናቱ የተወለደው የ18 ዓመቱ አማካይ በሁለት እጋጥሚዎች ወደ ፌይኖርድ ወጣት ቡድን እና ስቶኮልም ካደረጋቸው የውሰት ቆይታዎች ውጭ ላለፈት ዓመታት አሳዳጊ ክለቡን በተለያዩ የዕድሜ እርከኖች በማገልገል ላይ የቆየ ሲሆን አሁን ደግሞ ከክለቡ ጋር በመለያየት በኢንግሊዝ ቻምፕዮን ሺፕ ተሳታፊ ለሆነው ኪው ፒ አር ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።
ከጁርጋርደን ጋር የአንድ ዓመት ቀሪ ውል እያለው እያለው ክለቡን የለቀቀው ተጫዋቹ ወደ ኢንግሊዙ ክለብ ከማምራቱ በፊት ከዚህ በፊት ሌላው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ጌድዮን ዘላለም የተጫወበትን የስኮትላንዱ ሀያል ክለብ ሬንጀርስ ለመቀላቀል እጅጉን ተቃርቦ ነበር።