ኢትዮ ኤሌክትሪክ አማካይ አስፈረመ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ አማካይ አስፈረመ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ቤንች ማጂ ቡና ቆይታ የነበረው ወጣት አማካይ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቷል።

ከዚህ ቀደም በረከት ወልደዮሐንስ፣ ቤዛ መድህን እና ሀሰን ሑሴን አስፈርሞ የስምንት ነባር ተጫዋቾች ውል ያራዘመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሁን ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ ቤንቺ ማጂ ቡና ጥሩ ቆይታ ያደረገውን የተከላካይ አማካዩ ሀቢብ ጃለቶን አስፈርሟል።

የእግር ኳስ ሂወቱ በባቱ ከተማ ታዳጊ ቡድን ጀምሮ አሳዳጊ ክለቡ ባቱ ከተማን በሁለት አጋጣሚዎች እንዲሁም በሰንዳፋ በኬ እና ቤንጂ ማጂ ቡና መጫወት የቻለው ወጣቱ አማካይ በተጠናቀቀው ዓመት ከቤንጂ ማጂ ቡና ጋር ጥሩ የውድድር ዓመት ካሳለፈ በኋላ አሁን ደግሞ በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ወደ ሚሰለጥነው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቷል።