ሽመልስ በቀለ ወደ ግብፅ ይጓዛል

ሽመልስ በቀለ ወደ ግብፅ ይጓዛል

ከሀዋሳ ከተማ ጋር ዝውውሩን ያጠናቀቀው አማካዩ ሽመልስ በቀለ ወደ ግብፅ እንደሚጓዝ ተሰምቷል።

በቅርቡ ከተለያዩ ክለቦች ቆይታ በኋላ ወደ እናት ክለቡ ሀዋሳ ከተማ ለመጫወት ውሉን ያሰረው ስኬታማው ተጫዋች ሽመልስ በቀለ ወደ ግብፅ እንደሚጓዝ ሶከር ኢትዮጵያ መረጃ አግኝታለች።

ሽመልስ ወደ ግብፅ የሚያቀናው እንደከዚህ ቀደሙ ለግብፅ ክለብ ፊርማውን ለማኖር እንዳልሆነ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች። እንዳገኘነው መረጀ ከሆን ሽመልስ ወደ ግብፅ የሚጓዘው በቀጣይ ነሐሴ 30 በግብፅ ካይሮ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ ጋር ያለውን ጨዋታ ለመታደም እና ሀገሩን ለመደገፍ እንደሆነ ሰምተናል። ሽመልስ ወደ ግብፅ የሚጓዘው በራሱ ተነሳሽነት እና ሙሉ ወጪውን እራሱ በመሸፈን ጭምር እንደሆነ አውቀናል። ሽመልስ ዛሬ አመሻሽ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር አብሮ የሚጓዝ ይሆናል።

ሽመልስ ለግብፆቹ ክለቦች ፔትሮጀት (አምበል ) ፣ ኤል ጉና፣ ምስር አልመካሳ እና ኤንፒ በመጫወት የፕሮፌሽናል የእግርኳስ ሕይወቱን በግብፅ አስር ዓመት መምራቱ ይታወቃል።