ዋልያዎቹ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታቸው የሚያደርጉበት ሜዳ ታውቋል

ዋልያዎቹ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታቸው የሚያደርጉበት ሜዳ ታውቋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጣርያ ውድድሩን 9ኛ ጨዋታ የሚያደረግበት ስቴድየም ታውቋል።


በ2026 ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጣርያ ውድድሩ ሰባተኛ እና ስምንተኛ ጨዋታዎች ላይ ለመካፈል በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፤ ቡድኑ በቀጣይ ከሜዳው ውጭ ከግብፅ እና ከሴራልዮን ጋር ከሚያደርጋቸው ጨዋታዎች በኋላ ከጊኒ ቢሳው ጋር የሚያደርገው የማጣርያው ስምንተኛ ጨዋታም ኢትዮጵያ ባለሜዳ እንደሆነች ይታወቃል። በዚህም መነሻነት በፊፋ እውቅና የተሰጠው ሜዳ የሌላት ሀገራችን ከሁለት ወር በፊት በሩዋንዳ እንዲከናወን ለፊፋ አሳውቀው ፍቃድ እንዳገኙ የፌደሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ገልፀዋል።


ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች 1 ድል ፣ 3 አቻ እና 2 ሽንፈት አስተናግዶ በ6 ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ብሔራዊ ቡድናችን በቀጣይ ነሐሴ 30 ከግብፅ፤ ጳጉሜ 4 ደግሞ ከሴራሊዮን ጋር ከተጫወተ በኋላ መስከረም 26 ከጊኒ ቢሳው ጋር በሩዋንዳ እንዲሁም ጥቅምት 3 ከቡርኪና ፋሶ ጋር ተጫውቶ የማጣርያ ውድድሩን ያጠናቅቃል።