ዳዊት ተፈራ አዲስ ክለብ አግኝቷል

ዳዊት ተፈራ አዲስ ክለብ አግኝቷል

ከሁለት ክለቦች ጋር ሁለት የሊጉን ዋንጫ ከፍ ማድረግ የቻለው አማካዩ ዳዊት ተፈራ አዲስ ክለብ አግኝቷል።


በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ መድን ማሊያ የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ስኬታማ ቆይታን ያደረገው በቁመቱ ትንሽ የሆነው አማካይ ዳዊት ተፈራ ወደ አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ ማምራቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በሻሸመኔ ከተማ የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው ዳዊት በመቻል ፣ በጅማ አባቡና፣ በጅማ ከተማ፣ በሲዳማ ቡና ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ወደ ፈረሰኞቹ ቤት በመምጣት የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለ ሲሆን ዘንድሮ በተጠናቀቀው ውድድር ኢትዮጵያ መድን በታሪኩ ለመጀምርያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ በማስቻል ከፍተኛ አስተዋፆኦ ማድረግ ሲችል አሁን መዳረሻው ወደ አዲሱ የሊጉ ክለብ ነገሌ አርሲ ሆኗል።