ነገሌ አርሲ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል

ነገሌ አርሲ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል

ነገሌ አርሲን ከከፍተኛ ሊግ ያሳደጉትን አሰልጣኝ ውል በዛሬው ዕለት አድሷል።

በ2017 የከፍተኛ ሊግ ተሳትፎውን በምድብ ሀ ስር ተደልድሎ ሲወዳደር ቆይቶ ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቁ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆነው ነገሌ አርሲ ለቀጣዩ የሊግ ጉዞው ዘግየት ብሎም ቢሆን ያሳደጉትን የአሰልጣኝ በረከት ቱሉን ውል ማራዘሙን አውቀናል።

በባቱ ከተማ ብዙ ጊዜ ፕሮጀክት ላይ በመስራት የአሰልጣኝነት ህይወትን የጀመረው ወጣቱ አሰልጣኝ በረከት በመቀጠል በሼር ኢትዮጵያ ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ ከሰራ በኋላ በከፍተኛ ሊግ በባቱ ከተማ ረዳትም ዋና አሰልጣኝ በመሆን በማገልገል ዘንድሮ ነገሌ አርሲን ወደ ሊጉ እንዲያድግ ማድረጉ ይታወሳል።