የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለውን የመስመር ተጫዋችን አርባምንጭ ከተማዎች ለማስፈረም ተስማምተዋል።
በአሰልጣኝ በረከት ደሙ የሚመሩት ከቀናት በኋላ ወደ ቅድመ ዝግጅት የሚገቡት አርባምንጭ ከተማዎች የአብዛኛውን የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም እና የሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማምጣት ቡድኑን እያጠናከሩ ይገኛል። አሁን ደግሞ ሁለ ገቡን የመስመር ተጫዋች ኤፍሬም ታምራትን ለማስፈረም መቃረባቸውን አውቀናል።
በከምባታ ዱራሜ እግርኳስን መጫወት የጀመረው ኤፍሬም ቤንች ማጂ ቡና ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ ነበር ለኢትዮጰያ ንግድ ባንክ በመጫወት ራሱን ከሊጉ ጋር ያስተዋወቀው። ንግድ ባንክን በተቀላቀለበት ዓመት የሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ማንሳት የቻለው የግራ መስመር ተከላካይ እና የመስመር አጥቂ ሆኖ መጫወት የቻለው ኤፍሬም ከሁለት ዓመት ሀምራዊዎቹ ቤት ጋር ያደረገውን ቆይታ አጠናቆ አሁን መዳረሻው አዞዎቹ ቤት ሆኗል።