አዞዎቹ ናይጀርያዊን አጥቂ ለማስፈረም ተስማምተዋል

አዞዎቹ ናይጀርያዊን አጥቂ ለማስፈረም ተስማምተዋል

ቁመታሙ ናይጀርያዊ አዞዎቹን ለመቀላቀል ተስማማ

በአሰልጣኝ በረከት ደሙ የሚመሩት ቀደም ብለው የወሳኙ አጥቂያቸው አሕመድ ሔሴን፤ አማካዩ ይሁን እንደሻው እና ቶጋዊው ግብ ጠባቂ ኢድሪሱ ኢጎድጆ ጨምሮ የነባር ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ተስማምተው አማኑኤል ጎበናና ፅዮን መርዕድ ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት አርባምንጭ ከተማዎች አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በባህርዳር ከተማ ቆይታ የነበረው ቁመታሙ ናይጄርያዊ ጄሮም ፊሊፕን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የጣና ሞገዶቹ ቆይታው በ20 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1046′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው 1 ሜትር ከ92 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው የፊት መስመር ተሰላፊው በ2016 የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋለ ለኢትዮጵያ መድን እንዲሁም ለባህርዳር ከተማ የተጫወተ ሲሆን ከዛ በፊትም ለሀገሩ ክለቦች ጂ ሊች እና ዴሰርት ስታርስ እንዲሁም በግብፅ ክለቦችበሱኤዝ ፣ ስሞሀ፣ ዴክረንስ እና ካናህ ተጫውቶ አሳልፏል። አሁን ደግሞ ቀጣዩ መዳረሻው የአዞዎቹ ቤት ለማድረግ ከስምምነት ደርሷል።