አዞዎቹ ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

አዞዎቹ ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

በአሰልጣኝ በረከት ደሙ የሚሰለጥኑት አርባምንጭ ከተማዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅት መቼ እንደሚጀምሩ አውቀናል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በተሻሻለው በሊጉ የደረጃ ሰንረዥ መሠረት አርባምንጭ ከተማ በ55 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ መቻሉ ይታወቃል። የወሳኝ ነባር ተጫዋቾቹን ውል ማራዘም የቻሉ አዞዎቹ እስካሁን ከሀገር ውስጥ የግብ ጠባቂ ፅዮን መርድ እንዲሁም የአማኑኤል ጎበና ፣ ኤፍሬም ታምራት እና በኃይሉ ተስፋዬን ለማስፈረም የተስማሙ ሲሆን ከሀገር ውጪ ናይጄርያዊ አጥቂ ጄሮም ፊሊፕን የግላቸው ለማድረግ ተቃርበዋል። በቀጣዮቹም ቀናት ተጨማሪ የዝውውር ስራዎችን ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አሁን ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘቸው መረጃ ከሆነ ቡድኑ ወደ ዝግጅት የሚገባበትን ቀን አውቃለች። በዚህም ሰኞ ጳጉሜ 3 ቀን ጀምሮ የክለቡ አባላት በመቀመጫ ከተማ በሆነችው አርባምንጭ በመሰባሰብ በዛው የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ታውቋል።

የውድድሩ መቃረብ በመጣ ሰዓት የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ለማድረግ አሰልጣነኙ ጥረት እንደሚያደርጉም ሰምተናል።