ቢጫዎቹ የሦስት ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ተስማምተዋል።
በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙትና ከዚህ ቀደም የኪሩቤል ወንድሙ፣ ዳዊት ገብሩ፤ ናትናኤል ኪዳነ እና ናሆም ኃይለማርያምን ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት የደረሱት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ከሁለተኛ ቡድን አድገው በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ቡድኑን ያገለገሉ ሦስት ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።
ከአሳዳጊ ክለባቸው ጋር ለመቀጠል የተስማሙት ተጫዋቾች ደግሞ በተጠናቀቀው ዓመት በ15 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1076′ ደቂቃዎች ቢጫዎችን በመገልገል ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሱልጣን በርኸ፣ በ2011 አጋማሽ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ ባለፉት ዓመታት በዋናው ቡድን ደረጃ የተጫወተው እና በተጠናቀቀው ዓመት በ15 ጨዋታዎች ተሳትፎ ያደረገው የመስመር ተጫዋቹ ስምዖን ማሩ እንዲሁም በውድድር ዓመቱ በ13 ጨዋታዎች የተካፈለው አማካዩ ሚክኤለ ኪዳነ ከቢጫዎቹ ጋር ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ከስምምነት የደረሱ ተጫዋቾች ናቸው።