ተጠባቂው ጨዋታ በኢትዮጵያውን ዳኞች ይመራል

ተጠባቂው ጨዋታ በኢትዮጵያውን ዳኞች ይመራል

ራሱን ከዳኝነት ዓለም ለማግለል የወሰነው እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዳኞች ወደ ማፑቶ ያቀናሉ።

በምድብ ‘G’ የሚገኙትና አስራ ሁለት እና ዘጠኝ ነጥብ በመሰብሰብ ተከታትለው የተቀመጡትን ሞዛምቢክ እና ቦትስዋና የሚያደርጉት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ በኢትዮጵያውያን ዳኞች ይመራል። በጨዋታው የተመደቡት በቅርቡ ከዳኝነት ራሱን ያገለለው ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ፤ ኢንተርናሽናል ዳኛ ተመስገን ሳሙኤል እና ትግል ግዛው በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ በአራተኛ ዳኛነት ተመድበዋል።

ወሳኙ ጨዋታ በቀጣይ ሰኞ በማፑቶ ስታድዬ ዶ ዚምፔቶ ስታዲየም ሲካሄድ ዳኞቹም ነገ ወደ ሥፍራው ለማቅናት የአስፈላጊውን የጉዞ ሰነዶችን አሟልተው ቀኑን እየተጠባበቁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

* በተመደቡት ዳኞች ዙሪያ ተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎች ካሉ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።