የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ቢሳው እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ለ20 ተጫዋች ጥሪ አስተላልፈዋል።
በዝርዝሩ ዋንጫ ቱት፣ ኬኔዲ ከበደ፣ በረከት ካሌብ እና የ2017 የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ይታገሱ ታሪኩ የመጀመርያ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ የደረሳቸው ሲሆኑ ባልተለመደ ሁኔታ ለ20 ተጫዋቾች ብቻ ጥሪ መደረጉ ትኩረትን ስቧል።
ግብ ጠባቂዎች
አቡበከር ኑራ (ኢትዮጵያ መድን)
ቢንያም ገነቱ (ወላይታ ድቻ)
ተከላካዮች
ያሬድ ካሣዬ (ኢትዮጵያ መድን)
አሕመድ ረሺድ (ድሬዳዋ ከተማ)
ዋንጫ ቱት (ኢትዮጵያ መድን)
ኬኔዲ ከበደ (ወላይታ ድቻ)
ራምኬል ጀምስ (ኢትዮጵያ ቡና)
ንጋቱ ገብረሥላሴ (ኢትዮጵያ መድን)
በረከት ካሌብ (ኢትዮጵያ መድን)
አማካዮች
ሀብታሙ ተከስተ (ፋሲል ከነማ)
በረከት ወልዴ (ነገሌ አርሲ)
ሀይደር ሸረፋ (አዳማ ከተማ)
ወገኔ ገዛኸኝ (ኢትዮጵያ መድን)
ቢንያም አይተን (አዳማ ከተማ)
ይታገሱ ታሪኩ (ኢትዮጵያ ቡና)
አጥቂዎች
ቸርነት ጉግሳ (መቻል)
በረከት ደስታ (መቻል)
ኪቲካ ጅማ (መቐለ 70 እንደርታ)
አህመድ ሁሴን (አዳማ ከተማ)
መሐመድ አበራ (መቻል)
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች እሁድ መስከረም 18 እስከ 8:00 በጁፒተር ሆቴል ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንዲጀምሩ ፌዴሬሽኑ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ቢሳው ጋር በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በሩዋንዳው አማሆሮ ስታዲየም መስከረም 28፣ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ከቡርኪናፋሶ ጋር ዋጋዱጉ ላይ ጥቅምት 2 እንደሚያከናውን ተገልጿል።