ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ኩዊንስ አምርታ የነበረችው አማካይ ወደ ሀገር ቤት ተመልሳ ቻምፒዮኖችን ተቀላቅላለች።
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ላይ ጎልተው ከሚታዩ ተጫዋቾች መካከል አንዷ የሆነችው ማዕድን ሳህሉ በዚህ ዓመት መጀመሪያ በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለሚሰለጥነው የዩጋንዳው ካምፓላ ኩዊንስ ክለብ ለመጫወት ተስማምታ ወደ ስፍራው ብታቀናም ከሦስት ጨዋታዎች በኋላ ከቡድኑ ጋር ግልጽ ባልሆነ ምክንያት መቀጠል እንዳልቻለች ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
የቀድሞዋ የጥረት ኮርፖሬት ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና መቻል የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ላለፉት ሁለት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ከተጫወተች በኋላ ወደ ዩጋንዳ ብታመራም ብዙም ሳትቆይ ወደ ሀገር ቤት ተመልሳ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመጫወት ፊርማዋን አኑራለች።