የከፍተኛ ሊጉ ድምቀት አዲስ አዳጊዎችን ተቀላቅሏል

የከፍተኛ ሊጉ ድምቀት አዲስ አዳጊዎችን ተቀላቅሏል

ሸገር ከተማ ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረው የመስመር አጥቂ ወደ ሌላው አዲስ አዳጊው ክለብ አምርቷል።

በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ
ዳዊት ተፈራ፣ በረከት ወልዴ ፣ አብዱልባሲጥ ከማል ፣ ናትናኤል ሰለሞን እና ተስፋዬ በቀለን በማስፈረም የ14 ነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ዝግጅታቸውን በባቱ ከተማ እያደረጉ ያሉት ነገሌ አርሲዎች በመቀጠል የመስመር አጥቂውን ከቤ ብዙነህን ለማስፈረም መስማማታቸውን አውቀናል።

የአምቦ ጎል ፕሮጀክት ፍሬ የሆነው እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከሱሉልታ ክፍለ ከተማ ጋር ድንቅ የውድድር ዓመት ያሳለፈው ወጣቱ የመስመር አጥቂ አስቀድሞ ሸገር ከተማን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም አሁን መዳረሻው ነገሌ አርሲ ሆኗል።