ዳግማዊ አርአያ ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል

ዳግማዊ አርአያ ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል

ለሸገር ከተማ ለመፈረም ተስማምቶ የነበረው አጥቂው ወደሌላኛው አዲስ አዳጊ ክለብ አቅንቷል።

ያለፉትን ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ የነበው አጥቂው ዳግማዊ አርዓያ ከሰሞኑ አዲስ አዳጊዎቹን ሸገር ከተማን ለመቀላቀል ተስማምቶ የህክምና ምርመራውን በማድረግ ለቀናት ከቡድኑ ጋር ዝግጅት ሲያደርግ ቢቆይም ሳይጠበቅ ወደ ሌላኛው የሊጉ አዲስ ክለብ ነገሌ አርሲ ማምራቱ እርግጥ ሆኗል።


ያለፉትን ዘጠኝ ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ተጫውቶ ያሳለፈው ዳግማዊ ሁለት የፕሪሚየር ሊጉ እንዲሁም አንድ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ካነሳበት ክለቡ ጋር ዘንድሮ ውሉን ማጠናቀቁን ተከትሎ ከዓመታት ቆይታ በኋላ ለነገሌ አርሲ ለአንድ ዓመት ለመቆየት ተስማምቷል።