በሀገራችን የሚደረገው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር እጣ በነገው ዕለት ይወጣል

በሀገራችን የሚደረገው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር እጣ በነገው ዕለት ይወጣል

በድሬዳዋ እና አዲስ አበባ የሚደረገው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር የእጣ ማውጣት መርሐግብር በነገው ዕለት እንደሚከናወን ታውቋል።

ለ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማጣሪያ መርሐ-ግብር ሆኖ የሚያገለግለው የቀጠናው ፍልሚያ ከኅዳር 6 እስከ ኀዳር 23 ድረስ የሚከናወን ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም ውድድሩን ለማሰናዳት ቅድመ ዝግጅቷን እያከናወነች ትገኛለች።

ውድድሩ በድሬዳዋ እና አበበ ቢቂላ ስታዲየሞች እንደሚከናወን የተገለፀ ሲሆን ነገ በሚወጣው እጣም የወቅቱ የውድድሩ ቻምፒዮን ዩጋንዳ እና አዘጋጇ ኢትዮጵያ የምድብ አባት እንደሚሆኑ ተገልጿል። በዚህም በምድቡ አምስት አምስት ቡድኖች የሚደለደሉ ሲሆን አንደኛ እና ሁለተኛ የሚሆኑ ቡድኖች ወደ ግማሽ ፍፃሜ የሚያልፉ ይሆናል።

በውድድሩ አዘጋጇ ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡሩንዲ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ሱማሊያ፣ ኬኒያ እና ጂቡቲ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።