በኢትዮጵያ ዋንጫ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በዛሬው ዕለት በ10ኛ ሳምንት ጅማሮውን ሲያደርግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀዲያ ሆሳዕና ድል አድርገዋል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አርባምንጭ ከተማ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በዛሬው ዕለት ጅማሮውን ሲያደርግ በአሳቴዩ ስታዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከ አርባምንጭ ከተማ አገናኝቷል። ቀዝቀዝ ብሎ የጀመረ በሚመስለው ጨዋታ 27ኛው ደቂቃ ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች በፈጣን የመልሶ ማጥቃት ሽግግር ይዘው በገቡት ኳስ ላይ አዲስ ግደይ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት ራሱ አዲስ ግደይ ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል። በኢትዮ 31ኛው ደቂቃ ላይ ሳይመን ፒተር ከተከላካይ ጀርባ የተሻገረለትን ኳስ ከግብ ጠባቂ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ወደ ላይ ቺፕ አድርጎ የሞከረው ቢሆንም የግቡ አግዳሚን ገጭቶ ወጥቶበታል። አርባ ምንጭ ከተማዎች በበኩላቸው ይሄ ነው የሚባል ለግብ የቀረበ ሙከራን ሳያስመለክቱን በንግድ ባንክ መሪነት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።

ሀለተኛው አጋማሽ ላይ እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ ያልነበሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች በጥሩ ቅብብል ወደ ሳጥን ገብተው አዲስ ግደይ ያቀበለውን ኳስ ሳይመን ፒተር ግብ በማስቆጠር ድጋሚ ቡድኑን መሪ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል 86ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ፊሊሞን ገብሬ ከመስመር ያሻማውን ኳስ ሳይመን ፒተር በግንባሩ ቢሞክርም ግብጠባቂው ሳይመን ፒተር ወደ በጥሩ ብቃት ወደ ውጭ አውጥቶበታል ይህ ከሆነ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ 88ኛው ደቂቃ ላይ አሸናፊነታቸውን እርግጠኛ የሆኑበትን ግብ ሳይመን ፒተር ያቀበለውን ኳስ አዲስ ግዱይ ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑ 3-1 አሸናፊ ማድረግ ችሏል።

መቐለ 70 እንደርታን ከ ሀዲያ ሆሳዕና
በዕለቱ መርሐግብር የመጨረሻ ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታን ከ ሀዲያ ሆሳዕና ጋር ያገናኘ ሲሆን ተመጣጣኝ የሚባል እንቅስቃሴን ያስመለከቱን ሲሆን በኳስ ቁጥጥር ረገድ መቐለ 70 እንደርታዎች የተሻሉ ሲሆን ከራሳቸው የግብ ክልል ተደራጅተው ወደ ፊት በመጠጋት የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ሙከራ ሲያደርጉ በተቃራኒው ሀዲያ ሆሳዕናዎች በቆሙ እና በረጃጅም ኳሶች ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን 21ኛው እና 33ኛው ደቂቃ ላይ ሔኖክ አርፌጮ ከሳጥን ውጭ በሞከራቸው የቅጣት ምት ግብ የማግኘት ሙከራ ቢያደርጉም በግብ ጠባቂው ጥረት ግብ ከመሆን ድኗል።
36ኛው ደቂቃ ላይ መቐለ 70 እንደርታዎች መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ አስቆጥረዋል። መነሻውን ከማዕዘን ያደረገ እና በተጫዋቾች አለመግባባት እነሱን አልፎ ያገኘውን ዕድል ተመስገን ተስፋየ እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ቡድኑን መሪ ማድረግ የቻለበትን ኳስ አስቆጥሯል።

ከዕረፍት መልስ ግብ ለማግባት በጥሩ ጉጉት ወደ ሜዳ የተመለሱት ሀዲያ ሆሳዕናዎች 65ኛው ደቂቃ ላይ ከቆመ ኳስ የተሻገረውን ኳስ ቃለአብ ውብሸት በግንባር ገጭቶት የግቡ አግዳሚ የመለሰውን ኳስ ተመስገን ብርሃኑ በተለምዶ መቀስ ምት ተብሎ በሚጠራው መንገድ ድንቅ የሆነ ግብ በማስቆጠር ቡድኑን አቻ አድርጓል። ከዚህ ግብ መቆጠር በኋላ 75 ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያው ግብ ባለቤት ተመስገን ብርሃኑ ከሜዳው የግራ ክፍል መስመር ላይ ከርቀት እጅግ ድንቅ እና አስገራሚ በሆነ መንገድ ጠቅልሎ ግሩም የሆነ ግብ አስቆጥሯል። 83ኛው ደቂቃ ላይ የመቀሌ ግብ ባለቤት ተመስገን ተስፋየ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ይህንንም ተከትሎ ሀዲያ ሆሳዕና ከመመራት ተነስተው 2-1 በሆነ ውጤት መቐለ 70 እንደርታን አሸንፈዋል።


