አዞዎቹ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከጫፍ ደርሰዋል

አዞዎቹ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከጫፍ ደርሰዋል

በጊዝያዊ አሰልጣኝ እየተመራ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ተቃርቧል

በ2018 የውድድር ዘመን በአስራ ስድስት ሳምንታት
የሊጉ ጉዞ ድል ሳያስመዘግብ በደረጃ ሠንጠረዡ ግርጌ ላይ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ከአሰልጣኝ በረከት ደሙና የአሰልጣኞች ቡድን አባላቱ ጋር ከተለያየ በኋላ ያለፉትን ሰባት ጨዋታዎች በጊዝያዊ አሰልጣኝ አበባው ቡጣቆ እየተመራ መቆየቱ ይታወሳል።

ሆኖም የክለቡ ቦርድ ባደረገው ስብሰባ ቡድኑ በተፈለገው ልክ የውጤት መሻሻል ሊያስመዘግብ ባለመቻሉ ልምድ ያለው አሰልጣኝ መቅጠር አስፈላጊ መሆኑን በማመን ባለፉት ቀናት የተለያዩ አሰልጣኞችን የስራ ማስረጃ ሲገመግም ቆይቷል። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ከውስጥ ምንጮቿ ባገኘችው መረጃ መሰረት አዞዎቹ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳን ለመቅጠር መቃረባቸውን እና አሰልጣኙም የድርድሩን ሂደት ለማሳለጥ ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን አረጋግጣለች። ከዚህ በተጨማሪም ድርድሩ ምንም እንኳን ያልተጠናቀቀ ቢሆንም አሰልጣኙ ክለቡ ወደ አረፈበት ሆቴል በማምራት ስብስቡን ሊቀላቀሉ እንደሆነ ታውቋል። አሰልጣኝ አዲሴ ካሴ ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ፣ በስልጤ ወራቤ፣ ቡታጅራ ከተማ በቅርቡ ደግሞ በሲዳማ ቡና ማሰልጠናቸው ይታወቃል።