በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ የገባው ባካሪ ሳኛ በሊጉ ጨዋታ ላይ ይታደማል

በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ የገባው ባካሪ ሳኛ በሊጉ ጨዋታ ላይ ይታደማል

የቀድሞው የአርሰናል እና የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ባካሪ ሳኛ በሊጉ ጨዋታ ይታደማል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ይፋዊ የትጥቅ አቅራቢ ማክሮን የማብሰርያ መርሐግብር ላይ ለመታደም የቀድሞ የአርሰናል፣ ማንችስተር ሲቲ እና የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው ባካሪ ሳኛ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁንም በቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፍያ በመገኘት ለባካሪ ሳኛ አቀባበል ማድረጋቸው ይታወሳል።

ባካሪ ሳኛ ከሰዓት የዐድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን የጎበኘ ሲሆን በነገው ዕለትም በአዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታን እንዲታደም ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አውቀናል። ጥረቱ የሚሳካ ከሆነ ነገ ከሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ ተገኝቶ ከአድናቂዎቹ ጋር የኢትዮጵያ እግር ኳስን ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።