አርባምንጭ ከተማ 3-0 ኢትዮ ኤሌክትሪክ
15′ 31′ ተሾመ ታደሰ ፣ 90+2′ ሲሴይ ሀሰን
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
ጎልልል!!!! አርባምንጭ
90+2′ ሲሴይ ሀሰን ከግብ ጠባቂው ጋር ሳይናበብ ወደ ኀላ የመለሰው ኳስ ግብ ሆኗል፡፡
90′ መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪከ
75′ ምንተስኖት አበራ በታደለ መንገሻ ተቀይሮ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
69′ ማናዬ ፋንቱ ወጥቶ አብዱልሃኪም ሱልጣን ገብቷል፡፡
60′ የጨዋታው እንቅስቃሴ እንደመጀመርያው አጋማሽ መሆን አልቻለም፡፡ የግብ ሙከራም ሆነ የረባ እንቅስቃሴ እየታየ አይደለም፡፡
53′ ኤሌክትሪክ በኳስ ቁጥጥር የተሻሉ ቢሆኑም ወየ ተጋጣሚ የግብ ክልል መጠጋት አልቻሉም፡፡
50′ በረከት ተሰማ ከግብ ጠባቂው ጋር ተጋጭቶ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
ተጀመረ!!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት!!!
የመጀመርያው አጋማሽ በአርባምንጭ 2-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡
45+2′ ገብረሚካኤል በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ቢወድቅም የመሃል ዳኛው ጨዋታው እንዲቀጥል አዘዋል፡፡
ቢጫ ካርድ
44′ ማንክ ክዌሳ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
43′ ታደለ መንገሻ በግብ ጠባቂው አናት ላይ የሰደደው ኳስ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ተመልሷል፡፡ ግሩም ሙከራ ነበር፡፡
41′ ገብረሚካኤል 3ኛ ግብ ቢያስቆጥርም ኳሱን ሲቆጣጠር በእጁ ነክቷል በሚል ሳይፀድቅ ቀርቷል፡፡
37′ በጨዋታው እንቅስቃሴ ተመልካቹ እጅግ ደስተኛ ሆኗል፡፡ ታደለ እና እንዳለ በሚያሳዩት እንቅስቃሴ ሙገሳ እየተቸራቸው ይገኛል፡፡
ጎልልል!!!! አርባምንጭ
31′ እንዳለ ከበደ ያሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ተሾመ የአርባምንጭን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል፡፡
*** የታደለ ፣ እንዳለ ከበደ እና ገብረሚካኤል ጥምረት አስገራሚ ነው፡፡
*** የጨዋታው የእስካሁን እንቅስቃሴ መልካም የሚባል ነው፡፡
26′ ማንኮ ክዌሳ ከርቀት በግሩም ሁኔታ የሞከረውን ኳስ አንተነህ ወደ ውጪ አውጥቶበታል፡፡
18′ ከግቡ መቆጠር በኋላ ኤሌክትሪኮች ምላሽ ለመስጠት ሞክረዋል፡፡ ያገኙትን የቅጣት ምት በረከት ተሰማ መትቶ ግብ ጠባቂው አንተነህ ይዞበታል፡፡
ጎልልልል!!!! አርባምንጭ
15′ ተሾመ ታደሰ በጥሩ አጨራረስ አርባምንጭ ከተማን ቀዳሚ አድርጓል፡፡
ተጀመረ!!!
ጨዋታው ተጀምሯል፡፡
አርባምንጭ ከተማ
1 አንተነህ መሳ
2 ወርቅይታደል አበበ – 16 በረከት ቦጋለ – 4 አበበ ጥላሁን – 8 ትርታዬ ደመቀ
7 እንዳለ ከበደ – 18 አማኑኤል ጎበና – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 17 ታደለ መንገሻ
23 ተሾመ ታደሰ – 19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ
ተጠባባቂዎች
70 ጌድዮን መርዕድ
21 ምንተስኖት አበራ
6 ታሪኩ ጎጀሌ
20 አብይ በየነ
5 ሀብታሙ ወልዴ
13 አስቻለው ኡታ
14 አንድነት አዳነ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
1 አሰግድ አክሊሉ
5 አህመድ ሰኢድ – 21 በረከት ተሰማ – 26 ሲሴይ ሀሰን – 15 ተስፋዬ መላኩ
23 ማናዬ ፋንቱ – 4 ማንኮ ክዌሳ – 9 አዲስ ነጋሽ – 20 አሳልፈው መኮንን
16 ፍፁም ገብረማርያም – 28ፒተር ኑዋድኬ
ተጠባባቂዎች
22 ገመቹ በቀለ
7 አለምነህ ግርማ
24 ዋለልኝ ገብሬ
27 አሸናፊ ሽብሩ
8 በሃይሉ ተሻገር
17 አብዱልከሪም ሱልጣን
ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን!
የወራጅነት ስጋት ያንዣበበባቸው ሁለቱክለቦች በአንድ ነጥብ ልዩነት ተበላልጠው የዛሬውን ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡ የጨዋታው ውጤት የሁለቱን ቡድኖች የሊግ ጉዞ የሚወስን እንደመሆኑ ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡
ሶከር ኢትዮጵያም ጨዋታውን በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከአርባምንጭ ስታድየም ታደርሳችኋለች፡፡
መልካም ቆይታ!