ሀይቆቹ አጥቂ ለማስፈረም ተቃርበዋል

ሀይቆቹ አጥቂ ለማስፈረም ተቃርበዋል

ሀዋሳ ከተማዎች የዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ፈራሚያቸው ለማግኘት ተቃርበዋል

በቅርቡ ከሸገር ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየው አጥቂው ማረፊያው ሀይቆቹ ቤት ለመሆን ተቃርቧል፤ ወደ ሀዋሳ ከተማ ለማምራት ከስምምነት የደረሰው ተጫዋች ደግሞ አጥቂው አድናን ረሻድ ነው። በቅርቡ ከሸገር ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየው እና የሀዋሳ ከተማ የዝውውር መስኮቱ የመጀመርያ ፈራሚ ለመሆን ከጫፍ የደረሰው አጥቂው በአንቦ ፕሮጀክት ከተገኘ በኋላ በጅማ አባ ጅፋር እንዲሁም ለሁለት ዓመታት በአዳማ ከተማ ቆይታ በማድረግ ላለፉት ስድስት ወራት በሸገር ከተማ ከተጫወተ በኋላ አሁን ደግሞ መዳረሻው ሀዋሳ ከተማ ሊሆን ተቃርቧል።