አድናን ረሻድን ለማስፈረም የተቃረበው ሀዋሳ ከተማ የቀድሞው ተጫዋቹን አስፈረመ

በዘንድሮ የውድድር ዓመት ከወትሮ በተሻለ ሁኔታ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ በአጋማሹ እራሱን ለማጠናከር አጥቂውን አድናን ረሻድን ለማስፈረም የተቃረበ ሲሆን አሁን ደግሞ የቀድሞ ግብ ጠባቂው ዳግም ተፈራን አስፈርሟል። በሀዋሳ ከተማ በታዳጊ እና በዋናው ቡድን ግልጋሎት የሰጠው ግብጠባቂው በአዳማ ከተማ እና በመቻል ከተጫወተ ከዓመታት በኋላ ዳግም ወደ አሳዳጊው ክለብ መመለሱ እርግጥ ሆኗል።

