መቐለ 70 እንደርታዎች ናይጄርያዊውን ተጫዋች ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል

በሀያ ሁለት ነጥቦች 18ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት እና በቅርቡ በተዘጋው የውድድር ዓመቱ አጋማሽ የዝውውር መስኮት ቡድናቸውን ለማጠናከር አማካዩ ሀብታሙ ንጉሴን ያስፈረሙት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ናይጄርያዊውን ተጫዋች ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ደግሞ የፊት አጥቂው አይባሚ ፕሪንስ ኦፊሬ ነው፤ በሀገሩ ክለብ ዲኖ ስፖርት ክለብ ከተገኘ በኋላ በኢስራኤሉ ማካቢ አታ ቢያሊክ እና በሳይፕረስ ሊግ በሚሳተፈው አክሪታስ ክሎራካስ መጫወት የቻለው ይህ አንድ ሜትር ከሰማንያ አራት የሚረዝመው ግዙፍ አጥቂ አሁን ደግሞ ወደ ምዓም አናብስት ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።
ባለፉት ቀናት የጉዞ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በማጠናቀቅ ላይ የቆየው ወጣቱ ተጫዋች ከአንድ ቀን በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ዝውውሩን ያገባድዳል ተብሎ ይጠበቃል።

