የፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደራዊ ጉዳይ በተመለከት ምን አሉ?

የፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደራዊ ጉዳይ በተመለከት ምን አሉ?

👉  “ፍቃድ የተሰጠው ለአንድ ጨዋታ ብቻ ነው።”

👉 “የካፍ ገምጋሚ አካል ግብረ መልስ ተስፋ አስቆራጭ ነበር።”

👉 “ጨዋታው በዝግ እንዲሆን ደጋፊው እንዳይገባ…”

ዋልያው በድሬደዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከአምስት ዓመታት በኋላ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በሜዳው ያደርጋል ይህን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ባህሩ ጥላሁን በጉዳዩ  ዙርያ ተከታዮን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት ዕቅድ እንዳላት ይታወቃል። ይህ ዕቅዷ እውን እዳይሆን ሌላ ለማዘጋጀት ፍላጎት ያላቸው ሀገሮች ኢትዮጵያ ይህን ዕድል እንዳታገኝ እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት በሀገሯ የማጣርያ ጨዋታ የማታደርግ ሀገር እንዴት የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ትጠይቃለች የሚል ነበር። ይህን የእግርኳስ ፖለቲካን ለመመለስ ከአምስት ዓመት በኋላ በሀገራችን ጨዋታዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ስራ መሰራቱ  እና ይህን ሁኔታ መመቻቸቱ ለቀጣይ አፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድንችል ትልቅ ትርጉም አለው። ይሄም እንዲሳካ አቶ ኢሳያስ ጅራ ትልቁን ሚና ተወጥተዋል። የካፍ ገምጋሚዎች ወደ ድሬደዋ መጥተው ገምግመዋል ሙሉ የገምጋሚዎቹን ወጪ የሸፈነው ፌዴሬሽኑ ነው” ካሉ በኋላ በማስከተል

“የግምገማ ውጤቱን ሲገልፁ ግምገማው ተስፋ ስቆራጭ ነበር። ቀላል የምንለውን ነገሮች እነርሱ እንዲስተካከል ብለዋል ለምሳሌ የጎሉ አንግል ፣ ለየስታዲየሙ ፋሲሊቲ እና ሌሎች በስታዲየሙ ዙርያ እየተገነቡ ያሉ መሰረት ልማቶች ካልተስተካከለ ይህንን ጨዋታ የማናገኝበት ሁኔታዎች ተፈጥረው ነበር። ሆኖም የድሬደዋ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት የተባሉትን ነገሮች ለማስተካከል ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ጨዋታው ተፈቅዷል። የተፈቀደው ግን ለአንድ ጨዋታ ብቻ ነው። ጨዋታውም በቀን ብቻ እንዲደረግ እና ደጋፊ እንደይገባ በዝግ እንዲሆን ተወስኗል። በዚህ አጋጣሚ የድሬደዋ አስተዳደር አካላትን በፌዴሬሽኑ ስም ከልብ እናመሰግናል። ብለዋል።

በቀጣይ ከዚህ ጨዋታ ውጭ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎችን በሀገራችን ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን ጠቁመው አልፈዋል።