ዋልያዎቹ በወርሀዊው የፊፋ ደረጃ ከዘጠኝ ወራት በኋላ የደረጃ መሻሻል አግኝተዋል

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ሳኦቶሜ ፕሪንሲፔን በድምር ውጤት አራት ለባዶ በማሸነፍ ወደ ምድብ ማጣሪያው መሻገሩን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በፊፋ ወርሃዊ ደረጃ ሦስት ደረጃዎች በማሻሻል144ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠ። ባለፉት አምስት ወራት ይፋ በተደረጉ ወርሀዊ ደረጃዎች በተከታታይ በ147ኛ ደረጃ ላይ የነበሩት ዋልያዎቹ በቅድመ ማጣሪያ ውድድሩ ባገኟቸው ሁለት ድሎች ታግዘው ከዘጠኝ ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ደረጃቸው ከፍ ብሏል።

