ፕሪሚየር ሊግ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አሸናፊነት ሲመለስ ቡና ደረጃውን ወደ 2ኛ ከፍ አድርጓል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ሁሉም ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ድል ሲመለስ ኢትዮጵያ ቡና ደደቢትን በመርታት ወደ 2ኛ ደረጃ መጥቷል፡፡ በግብ ድርቅ ተመትቶ የሰነበተው የኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግም በዚህ ሳምንት ነፍስ የዘራ መስሏል፡፡

ወደ ሀድያ የተጓዘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዲያ ሆሳዕናን 2-0 በመርታት ወደ ዋንጫው የሚያደርገውን ግስጋሴ ቀጥሏል፡፡ ባለፈት 2 ጨዋታዎች ድል ሳያስመዘግብ ርቆ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ድል የተመለሰባቸውን 2 ግቦች ሳላዲን ሰኢድ በ33ኛው እና 85ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አዋህዷል፡፡ ድሉ ቅዱስ ጊዮርጊስ 40 ነጥብ በመያዝ 7 ጨዋታዎች ብቻ በቀሩት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከተከታዩ ኢትዮጵያ 9 ነጥቦች ርቆ እንዲቀመጥ ሲያደርገው ሀዲያ ሆሳዕና ወደ ከፍተኛ ሊጉ የመመለሻ መንገዱን ተያይዞታል፡፡
ከጨዋታው በኋላ የሀዲያ ሆሳዕና ደጋፊዎች በተስፋ መቁረጥ ስሜት ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ግጭት የፈጠሩ ሲሆን ፖሊስም ግርግሩን ለማረጋጋት አሰለቃሽ እስከመጠቀም ደርሷል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ደደቢትን ከጨዋታ የበላይነት ጋር 3-0 በማሸነፍ ወደ 2ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል፡፡ በፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ ጨዋታውን የጀመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በሳዲቅ ሴቾ የ2ኛው ፣ 16ኛው እና 84ኛ ደቂቃ ግቦች 30 በሆነ ውጤት ሲያጠናቅቁ በቅርቡ ወደ ቋሚ አሰላለፍ የመጣው ሳዲቅ ሴቾም በቡና ማልያ የመጀመርያ ግቡን እና ሐት-ትሪክ ማስመዝገብ ችሏል፡፡ የሳዲቅ ሐት-ትሪክ ከኤዶም ሆሶውሮቪ በመቀጠል የውድድር ዘመኑ 2ኛ ሐት-ትሪክ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የ1ኛውን ዙር 9ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ቡና በ2ኛው ዙር ተሸሽሎ በመቅረብ 2ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

PicsArt_1463164744173

በወራጅነት ስጋት ውስጥ የሚገኙት አርባምንጭ ከተማ እና ኤሌክትሪክ ባደረጉት ጨዋታ አርባምንጭ 3-0 አሸንፎ ወራጅ ቀጠናውን ለኤሌክትሪክ አስረክቧል፡፡ ከአርባምንጭን የድል ግቦች ሁለቱን ተሾመ ታደሰ ሲያስቆጥር አንዱን ግብ ሴራሊዮናዊው ሲሴይ ሀሰን ኮማን በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ መከላከያን አስተናግዶ 2-0 አሸንፏል፡፡ የሀዋሳ ከተማን የድል ግቦች ከመረብ ሳረፉት ሙጂብ ቃሲም እና ፍርዳወቅ ሲሳይ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ወደ ጎንደር የጓዘው አዳማ ከተማ ተሸንፎ ከመሪው ያለውን ርቀት አስፍቷል፡፡ ዳሽን ቢራ 1-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ብቸናዋን ግብ ናጄርያዊው አጥቂ መሃመድ ሸሪፍ ዲን ከመረብ አሳረፏል፡፡

ወደ ድሬዳዋ የተጓዘው ድቻ በአቻ ውጤቱ ቀጥሎ ካለግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ ጥሩ ግስጋሴ እደረገ የነበረው ድሬዳዋ ከተማ ወደ ሰንጠረዡ አናት የመጠጋት እድሉን ሲያመክን ወላይታ ድቻ ለ5ኛ ተከታታይ ጨዋታ ካለግብ አቻ ተለያይቷል፡፡

ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አስተናግዶ 1-1 ተለያይቷል፡፡ ኬንያዊው ኤሪክ ሙራንዳ በ14ናው ደቂቃ ሲዳማን ቀዳሚ ሲያደርግ ቶክ ጀምስ በ79ኛው ደቂቃ ላይ ንግድ ባንክን አቻ አድርጓል፡፡

 

የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1463163800098

የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ

PicsArt_1463163851398

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *