ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሀይቆቹ ቤት ቆይታ የነበረው ሰዒድ ሀብታሙ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል።

በጅማ አባቡና ፣ ወልቂጤ ከተማ፣ አዳማ ከተማ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ሲያገለግል የቆየው ግብጠባቂው ሰዒድ ሀብታሙ ከሀዋሳ ጋር የነበረው ውል መጠናቀቁ አይዘነጋም። ላለፉት ሦስት ሳምንታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ የሚገኘው ግብ ጠባቂው ከሐይቆቹ ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ማረፊያው ነገሌ አርሲ ለመሆን መስማመቱን አውቀናል። ግብ ጠባቂው ሰዒድ በሰጎኖቹ ቤት ለሁለት ዓመት ለማቆየት መስማማማቱንም አውቀናል።

