እንየው ካሳሁን አዲስ ክለብ አገኘ

እንየው ካሳሁን አዲስ ክለብ አገኘ

የቀኝ መስመር ተከላካዩ እንየው ካሳሁን አዲስ ክለብ አግኝቷል።

በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚመሩት እና በዝውውር መስኮቱ አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርመው የበርካታ ነባር ተጫዋቾች ውል ያራዘሙት ኢትዮጵያ መድኖች አሁን ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላካዩ እንየው ካሳሁንን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ከዚህ ቀደም በፌዴራል ፖሊስ፣ አዲስ አበባ ከተማ፣  ወልዋሎ፣ ፋሲል ከተማ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና በሀዋሳ ከተማ መጫወት የቻለው ተጫዋቹ  ኢትዮጵያ መድንን ለመቀላቀል ከተስማማ በኋላ በዛሬው ዕለት የሕክምና ምርመራው ያደረገ ሲሆን ከቀጣይ ቀናት ዝውውሩ በይፋ ካጠናቀቀ በኋላ ከአንድ ዓመት በኋላ ዳግም ወደ ፕሪምየር የሚመለስ ይሆናል።