👉 “ይቅርታ እንጠይቃለን ፤ በፍጥነት እናስተካክላለን” አቶ ኢሳይያስ ጅራ

👉 “ይቅርታ እንጠይቃለን ፤ በፍጥነት እናስተካክላለን” አቶ ኢሳይያስ ጅራ

👉 “ይቅርታ እንጠይቃለን ፤ በፍጥነት እናስተካክላለን” አቶ ኢሳይያስ ጅራ

ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ዛሬ ከትሪቡን ስፖርት ጋር ልዩ ቆይታ ያደረጉት አቶ ኢሳይያስ ጅራ ምን አሉ?

የወቅቱ መነጋገርያ ርዕስ የሆነው በዋናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በሚዲያ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ በመጣበት በአሁኑ ወቅት ፌዴሬሽኑ ያወጣውን የአሰራር ስርዓት ተከትሎ ዛሬ ሚዲያዎች ሰዓቱን አክብረው በቦታው ቢገኙም እንዳይዘግቡ መደረጉ ይታወሳል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከሰዓት ላይ በብሥራት ኤፍ ኤም በሚተላለፈው ትሪቡን ስፖርት ላይ አቶ ኢሳይያስ ጅራ በቀጣይ አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በሚመሩበት ወቅት ሊሰሩ ያሰቧቸውን ዕቅዶች ሲያብራሩ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል

“ከሚዲያ ጋር ተያይዞ እንደ ተቋምም እንደ ግለሰብም ችግር ያለብን አይመስለኝም። አንድ አንድ ክፍተቶች ከብሔራዊ ቡድን ጋር ተያይዞ የሚነሱ አሉ እነርሱን የምናስተካክል ይሆናል። ትናንትናም አንስቻለሁ። ዛሬም የተፈጠሩ ነገሮች ስላሉ ይቅርታ እንጠይቃለን በፍጥነት እናስተካክላለን።”