👉 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ለመሆን ጠንካራ ስራ ይጠብቅናል

👉 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ለመሆን ጠንካራ ስራ ይጠብቅናል

የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት እና ከሚዲያ ጋር እየተፈጠረ ያለው መራራቅ …

ለሦስተኛ ጊዜ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት ብቸኛ ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት አቶ ኢሳያስ ጅራ እየሰጡት ያለው ጋዜጣዊ መግለጫ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። በቦታው የሚገኙት የመገናኛ ብዙኀን ባለሞያዎች እንደተሰጣቸው ዕድል ጥያቄያቸው በማቅረብ ላይ የሚገኙ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ እንደሚቀከተለው አቅርበናል።

የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት እና በሚዲያ ግንኙነት ዙርያ ልዩነት እየሰፋ ነው ፤ ይህ ለማስተካከል ምን ያስባሉ ?

“ብሔራዊ ቡድኑን በተመለከተ አሁን ምንም ማለት አልፈልግም። ትክክለኛ ጥያቄ ነው የቀረበው እንደ ግብአት እንወስደዋለን በትክክል እናስተካክላለን”ብለዋል

የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት በተመለከተ ?

የ2028 የአፍሪካ ዋንጫን ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። አስፈላጊውን ሰነድ አስገብተናል። በእኛ በኩል የተጀመሩትና ያላለቁ ስታዲየሞች ለማጠናቀቅ እየተሰራ ያለው ስራ እንዳለ ሆኖ ስድስት ስታዲየሞችን እና አስራ አምስት የልምምድ ሜዳዎችን ለመስራት በመንግስት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን አዘጋጅ ሀገር ለመሆን ጠንካራ ስራ ይጠብቅናል። በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።