ቴክኒክ ማዕከል ለመገንባት ሱሉልታ ከተማ ላይ 10 ሔክታር መሬት አግኝተናል

ቴክኒክ ማዕከል ለመገንባት ሱሉልታ ከተማ ላይ 10 ሔክታር መሬት አግኝተናል

“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከታች ጀምሮ ጠንካራ የሆነ ተፎካካሪ የሆነ ቡድን ለመገንባት አስባለው”

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፉት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በብቸኝነት እጩ ሆነው መቅረባቸው ተከትሎ በዚሁ ጉዳይ እና የእሳቸው የካቢኔ አባላት ስላሰቧቸው ተግባራት እንዲሁም በሚነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት በአሁኑ ሰዓት ወሎ ሰፈር በሚገኘው ቤስት ዌስተርን ሆቴል የጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል። በመግለጫቸውም በቀጣይ አራት ዓመት ለመስራት ያሰቡትን ሲናገሩ

በቀጣይ አራት ዓመታት ውስጥ ለመስራት በአስር ፒላር ላይ ቆመው ከሚመለከታቸው የመንግስት እና የስፖርት ፌዴሬሽን አካላት በጋራ በመሆን ፌዴሬሽኑ የራሱ ቴክኒክ ሴንተር እንዲኖረው ማድረግ ዋና ዕቅዳቸው እንደሆነ ገልፀው “ብሔራዊ ቡድኑ ልምምድ የሚሰራበት የራሱ የሆነ ሜዳ የለም፤ ይህን ለመቅረፍ ሱሉልታ ከተማ ላይ ወደ አስር ሔክታር መሬት አግኝተናል። ምስጋና ለኦሮምያ ፕሬዝደንት ሽመልስ አብዲሳ ይግባውና በቀጣይ አጠቃላይ ስራውን ለመስራት ኦቪድ ቃል ገብቶልናል። በቀጣይ ትልቅ መሰረት እንጥላለን ብለን እናስባለን። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከታች ጀምሮ ጠንካራ የሆነ ተፎካካሪ የሆነ ቡድን ለመገንባት አስባለው” ብለዋል።