የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚ ከማጣሪያ ውድድሩ ራስዋን አገለለች

በአፍሪካ ዋንጫ ከ23 ዓመት በታች ማጣሪያ ውድድር ከኢትዮጵያ ጋር የተደለደለው የዩጋንዳ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከማጣሪያ ውድድሩ ራሱን ማግለሉ የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን አድርጓል። የሀገሪቱ መንግስት የዩጋንዳ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ለ2027 አፍሪካ ዋንጫ ለሚያደርገው ዝግጅት የበጀት ቅድሚያ በመስጠቱ ይህ ውሳኔ መወሰኑም ታውቋል።
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት ብሔራዊ ቡውን በማጣሪያ ውድድሩ በቀጥታ ከሞሮኮ አቻው ጋር የሚጫወት ይሆናል።

