ጋናዊው ግብ ጠባቂ በሀዲያ ሆሳዕና ቤት ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ተስማምቷል።

በአሰልጣኝ ሳምሶም አየለ እየተመሩ ቅደመ ውድድር ዝግጅታቸውን በመቀመጫ ከተማቸው ከቀናት በፊት የጀመሩት ሀዲያ ሆሳዕናዎች የወሳኝ ግብ ጠባቂያቸውን አንድሪውስ ኦውሱን ውል ማራዘማቸውን አውቀናል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ሀገራችን ከመምጣቱ በፊት በሀገሩ ክለብ አክራ ላዮንስ የአራት ዓመት ቆይታ ካደረገ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ሞልዶቫ አቅንቶ በሀገሪቱ ‘ሱፐር ሊጋ’ ተሳታፊ በነበረው ሲ ኤስ ኤፍ ስፓርታኒ ስፖርቱል ሰሌመት ቆይታ የነበረው ወጣቱ ግብ ጠባቂ አንድሪውስ ኦውሱ አሁን ለተጨማሪ አንድ ዓመት ከቡድኑ ጋር የሚቆይበትን ውል ማራዘሙን ክለቡ በላከልን መረጃ አረጋግጠናል።

