ማላዊው ተከላካይ ወደ ጋሞ ጨንቻ አመራ

ማላዊው ተከላካይ ወደ ጋሞ ጨንቻ አመራ

አዲስ አዳጊዎቹ ስብስባቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል

ቀደም ብለው ናይጄርያዊው አማካይ ቤሎ ማርቲንስ እና ቻዳዊው ግብ ጠባቂ ምባይናሰም ጆርዲንን ያስፈረሙት አዲስ አዳጊዎቹ ጋሞ ጨንቻዎች አሁን ደግሞ የማሊ ዜግነት ያለው ተከላካይ አስፈርመዋል። ወደ ቡድኑ የተቀላቀለው የመሀል ተከላካዩ ቤካዬ ዲያኪቲ ነው፤ ከዚህ ቀደም በማውሪታንያው ቼማል ጨምሮ በአይቮሪኮስት በሚገኙ ክለቦች ስቴላ ክለብ ዲአጃሜ እና ኤል ዋይ ኤስ ሳሳንድራ እንዲሁም በቶጎው ክለብ ‘ASKO de Kara’ መጫወት የቻለው ተከላካዩ አሁን ደግሞ ወደ አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ አምርቷል።