አዳማ ከተማ ዮሴፍ ታረቀኝን አስፈረመ

አዳማ ከተማ ዮሴፍ ታረቀኝን አስፈረመ

የፊት መስመር ተጫዋቹ ዳግም ወደ እናት ክለቡ ተመለሰ።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች በቅርቡ ከሸገር ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየውን የቀድሞ ተጫዋቻቸው ዮሴፍ ታረቀኝን አስፈረሙ። የእግርኳስ ህይወቱን በአዳማ ከተማ ጀምሮ በክለቡ በታዳጊ እና ዋናው ቡድን ደረጃ ማገልገል የቻለው የ2015 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ወጣት ተጫዋች የነበረው ዮሴፍ ከአሳዳጊ ክለቡ አዳማ ከተማ ከተለያየ በኋላ በሀዋሳ ከተማ ፣ መቻል እንዲሁም ሸገር ከተማ መጫወት ቢችልም በሦስቱ ክለቦች በተመሳሳይ ውሉን ሳያገባድድ ተለያይቶ ከዓመታት በኋላ ዳግም ወደ እናት ክለቡ አዳማ ከተማ ተመልሷል።