የአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ ረዳቶች ታውቀዋል

የአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ ረዳቶች ታውቀዋል

አመለ ሸጋው የአንድ ክለብ ሰው ሀሰን በሽር
ከ30 ዓመት በላይ በቆየበት ቤት ለመቀጠል ሲስማማ ሀፍቶም ቢሰጠኝ ወደ አሰልጣኝነት ገብቷል

በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ እየተመሩ ለ2019 የውድድር ዓመት በአዳማ ከተማ ቅድመ ዝግጅታቸው በማከናወን ላይ የሚገኙት በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚመሩት ኢትዮጵያ መድኖች የቡድኑ ረዳቶች አሳውቀዋል።

መተሐራ ያፈራችውና በ1990 የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን ያጠናቀቀው እና በተጫዋችነት ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን እንዲሁም በአሰልጣኝነት ኢትዮጵያ መድንን ከ30 ዓመታት በላይ በታማኝነት ያገለገለው አመለ ሸጋው ሀሰን በሽር ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል።

በተለያዩ ውድድሮች ላይ የሀገሩን ስም ያስጠራው የስመ ገናናው ብስክሌተኛ ደስታ ቢሰጠኝ ታናሽ ወንድም የሆነው ሀፍቶም ቢሰጠኝ ደግሞ የኢትዮጵያ መድን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆኗል። ሀፍቶም በተጫዋችነት በትራንስ ኢትዮጵያ ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና በደደቢት እንዲሁም በወጣት ብሔራዊ ቡድን በግብ ጠባቂነት ማገልገሉ ይታወቃል።