ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ አንድ ተጫዋች በጉዳት ወጥቷል

ከሱዳን እና ከሴኔጋል ጋር ላለባቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙት እና ላለፉት አስራ አንድ ቀናት ልምምድ በማድረግ ላይ ያሉት ዋልያዎቹ በጉዳት ምክንያት አንድ ተጫዋች ማጣታቸው ታውቋል። ጉዳት የገጠመው ተጫዋች ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሄኖክ አዱኛ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ መሰረት ተጫዋቹ ሰሞኑ እግሩ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ጋር አብሮ እንደማይገኝ አውቀናል። ባደረግነው ማጣራት ደግሞ ጉዳቱ ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጭ ሳያደርገው እንዳልቀረ ከምንጮቻችን አረጋግጠናል።

