ዩጋንዳዊው ወደ አዳማ ከተማ ለማቅናት ተስማማ

ዩጋንዳዊው ወደ አዳማ ከተማ ለማቅናት ተስማማ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከዐፄዎቹ ጋር ቆይታ የነበረው ተከላካይ ወደ አዳማ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

ፋሲል ተካልኝን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩት እና እንደ ሌሎች የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ ያላደረጉት አዳማ ከተማዎች ቀደም ብለው በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበራቸው አሰጋኸኝ ጴጥሮስ ፣ ፍፁም ዓለሙ እና ቦና ዓሊ እንዲሁም  ይሁን እንደሻው ማስፈረማቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ዳግሞ ዩጋንዳዊው ዋሳዋ ጂኦፍሪ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ከዚህ በሀገሩ ክለቦች ካምፓላ ሲቲ ፣ ቫይፐርስ እና በኤስ ሲ ቪላ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ወደ ሀገራችን መጥቶ በኢትዮጵያ ቡና እና በፋሲል ከነማ የአንድ አንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው የመሀል ተከላካዩ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ31 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2970′ ደቂቃዎች ዐፄዎቹን ማገልገሉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ አዳማ ከተማን ለመቀላቀል ተስማምቷል።