ወልዋሎ የተከላካዩን ውል አራዘመ

ወልዋሎ የተከላካዩን ውል አራዘመ

ጌቱ ኃይለማርያም ከቢጫዎቹ ጋር ለመቀጠል ውሉን አራዝሟል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሽ ሻሸመኔ ከተማን ለቆ ወደ ወልዋሎ በማምራት ላለፉት ስድስት ወራት በቢጫዎቹ ቤት ቆይታ የነበረው የመስመር ተከላካዩ ጌቱ ኃይለማርያም በዛሬው ዕለት ውሉን አራዝሟል። ቀሪ የስድስት ወር ውል እያለው ለተጨማሪ ስድስት ወራት ውሉን ያራዘመው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በሰበታ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ሻሸመኔ ከተማ እንዲሁም በወጣት ብሔራዊ ቡድን መጫወቱ ይታወሳል።