ወደ ዋናው ቡድን ካደገበት ጊዜ አንስቶ ለቡናማዎቹ ጥሩ ግልጋሎት እየሰጠ ያለው በፍቃዱ አለማየሁ ፊርማውን አኑሯል

በአሰልጣኝ ገብረመድን ሀይሌ እየተመሩ በአዳማ ከተማ ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እያከናወኑ ያሉት ኢትዮጵያ ቡናዎች ወሳኝ ተጫዋቻቸው በፍቃዱ አለማየሁን ለተጨማሪ ዓመት በቡድኑ ለማቆየት ውሉን አራዝመውለታል።
ከታዳጊ ቡድን የተገኘው እና በመስመር ተከላካይ እንዲሁም የመስመር አጥቂ ሆኖ መጫወት የሚችለው በፍቃዱ በተጠናቀቀው ዓመት በ33 ጨዋታዎች 2834 ደቂቃዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ ሦስት ጎሎችን በማስቆጠር ጥሩ ጊዜን ማሳለፈፉ ይታወቃል። ተጫዋቹ ምንም እንኳን በውሉ ላይ ቀሪ ስድስት ወራት ቢኖረውም በአዲስ መልክ ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት የሚያቆየውን ስምምነት መፈፀሙን አውቀናል።

