በኃይሉ ግርማ  አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተስማማ

በኃይሉ ግርማ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተስማማ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በምድረ ገነት ሽረ ቆይታ የነበረው አማካይ ወደ ሌላው የሊጉ ክለብ ለማምራት ተቃርቧል

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሽረ ምድረ ገነትን በአምበልነት እየመራ ቆይታ ያደረገው አማካዩ በኃይሉ ግርማ ወደ አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል። በአዲስ አሰልጣኛቸው ካሊድ መሐመድ እየተመሩ ለቀጣይ የውድድር ዓመት ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙት እና በዝውውር መስኮቱ ቡድናቸውን ለማጠናከር ተሳትፎ ያደረጉት በርበሬዎቹ አሁን ደግሞ አማካዩ በኃይሉ ግርማ ለማስፈረም የተስማሙ ሲሆን አማካዩም በዚህ ሰዓት ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል መንገድ ላይ እንደሚኝ አውቀናል።

ከሙገር ሲሚንቶ በኋላ ወደ መቻል አምርቶ በሁለት አጋጣሚዎች ጦሩን ለሰባት ዓመታትን ማገልገል የቻለው በኃይሉ ከዚህ ቀደም በሰበታ ከተማ እንዲሁም በተጠናቀቀው ዓመት በሽረ ምድረ ገነት መጫወት የቻለ በርካታ ክለቦችን በአምበልነት የመራ ተጫዋች መሆኑም ይታወሳል።