የኢትዮዽያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል

ዛምቢያ ለምታስተናግደው የአፍሪካ ከ20 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ጋናን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ዝግጅቱን ቀጥሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የጀመረው ዝግጅት እስከ ሐሙስ ድረስ በአዲስ አበባ ስቴድየም የቀጠለ ሲሆን የአዲስ አበባ ስቴዲዮም በዝናብ ምክንያት በመጨቅየቱ አርብ እና ቅዳሜ በጃንሜዳና ሱሉልታ ልምምድ ሰርተዋል፡፡ እሁድን እረፍት በማድረግም ከዛሬ ከሰኞ ጀምሮ በሚጫወቱበት ሜዳ በአዲስ አበባ ስቴዲዮም ልምምድ መስራታቸውን ቀጥለዋል፡፡

በዛሬው የልምምድ ፕሮግራም ቀለል ያለ ልምምድ የሰሩ ሲሆን በፌዴሬሽኑ የህክምና ባለሙያ የተወሰኑ ተጨዋቾች ላይ የMRI ምርመራ ሲደረግላቸው ለማየት ችለናል፡፡

አቡበከር ሳኒ እና ደስታ ዮሐንስ ብሔራዊ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ጥሪ የተደረገላቸው ባሳለፍነው ሳምንት ቢሆንም ከቡድኑ ጋር ተቀላቅለው ልምምድ የጀመሩት ዛሬ ነው፡፡

 

የተጨመሩ እና የተቀነሱ …

ከሻሸመኔ ከተማ ከተጠሩት 4 ተጫዋቾች መካከል ጫላ ተሻገር ብቻ የቀረ ሲሆን ውብሰት ስዩም ፣ ፀጋ ጎሳዬ እና ብርሃኑ በቀለ ተቀንሰዋል፡፡ ቡድኑ ማክሰኞ ከኢ/ወ/ስ አካዳሚ ጋር ባደረገው ጨዋታ ምርጥ ብቃቱን ያሳየው ግብ ጠባቂው ጆቤድ ተጠርቶ ከረቡዕ ጀምሮ ልምምድ ሰርቷል፡፡

በአሁኑ ሰአት በቡድኑ ውስጥ 28 ተጫዋቾች የሚገኙ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ቁጥሩ ወደ 25 ዝቅ ይላል፡፡

PicsArt_1463429253709

የኢትዮጵያ እና ጋና ጨዋታ በመጪው እሁድ 10:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም የሚካሄድ ሲሆን የጋና ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *