ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ የአልጄርያው ኤምኦ ቤጃያ የቱኒዝ ክለቦችን መጣሉን ሲቀጥል ማዜምቤ ወደ ምድብ ድልድል

-በአምላክ እና ኢትዮጵያውያን ረዳቶቹ ዛሬ ያጫውታሉ፡፡

 

የኦሬንጅ ካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ አላፊ ክለቦች ማክሰኞ ዕለት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች መታወቅ ጀምረዋል፡፡

የአልጄሪያው ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ የቱኒዚው ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝን ከሜዳ ውጪ በተቆጠረ ግብ በመጣል ወደ ምድብ ድልድሉ ማለፍ ችሏል፡፡ ቤጃያ በቻምፒየንስ ሊጉ የቱኒዙን ክለብ አፍሪካን ከውድድር ያስወጣ ሲሆን አሁን ደግሞ ሌላኛው ታላቅ የቱኒዝያ ክለብ ከውድድር አስወጥቷል፡፡

ቤጃያ ላይ ሁለቱ ክለቦች ካለግብ አቻ በመለያየታቸው በመልሱ ጨዋታ ቱኒዝ ላይ ኤስፔራንስ የማለፍ ቅድሚያ ግምቱን አግኝቶ ነበር፡፡ አንድ አቻ በተጠናቀቀው ጨዋታ ኤስፔራንስ በ9ኛው ደቂቃ ሸምሰዲን ዳዉዲ የፍፁም ቅጣት ምት ያመከነ ሲሆን በጋሊያን ቻላሊ ግብ መምራት ችሎ ነበር፡፡ የቤጃያ ሴኔጋላዊ አጥቂ መሃመድ ንዶይ የቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ሁለተኛ ግብ ጠባቂ የሆነው ሞይዝ ቤን ሻሪፍ የሰራውን ስህተት ተጠቅሞ የአቻነቷን ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡

13233197_825499074247929_716799884_n

የዲ.ሪ. ኮንጎው ቲፒ ማዜምቤ ጋቢሲየን ላይ ከባድ ፈተና ቢገጥመውም ወደ ምድብ ድልድሉ ከማለፍ አላገደውም፡፡ በኮንፌድሬሽን ካፑ ጥሩ ጉዞ ያደረገው የቱኒዚያው ስታደ ጋቢሲየን በሜዳው 2-1 ማሸነፍ ቢችልም ከሁለት ሳምንት በፊት ሉቡምባሺ ላይ በጆናታን ቦሊንጊ ግብ 1-0 በመሸነፉ ወደ ምድብ ድልድሉ ሳይገባ ቀርቷል፡፡ የየሱፍ ፋውዚ ፍፁም ቅጣት ምት ግብ ጋቢሲየንን መሪ ሲያደርግ ቦሊንጊ በሁለተኛው አጋማሽ አቻ ማድረግ ችሏል፡፡ አህመድ ዚግዛግ ሆስኒ የጋቢሲየንን ሁለተኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ቦሊንጊ ግብ ካስቆጠረ በኃላ የጋቢሲየን ተጫዋችን በክርን በመማታቱ ከሜዳ በቀይ ካርድ ወጥቷል፡፡

ወደ ምድብ ማጣሪያ ለማለፍ የሚደረጉት ጨዋታዎች ዛሬ ፍፃሚያቸውን ያገኛሉ፡፡ ጋቦን ሊበርቪል ላይ በሲኤፍ ሞናና እና በ2015 ኮንፌድሬሽን ካፕ አሸናፊው ኤቷል ደ ሳህል መካከል የሚደረገውን ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል የመሃል ዳኛ ባምላክ ተሰማ፣ ረዳቶቹ ክንዴ ሙሴ እና ተመስገን ሳሙኤል ይመሩታል፡፡

የማክሰኞ ውጤቶች

ስታደ ጋቢሲየን (ቱኒዚያ) 2-1 ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) [2-2]

ኤስፔራንስ ስፖርቲቭ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) 1-1 ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (አልጄሪያ) [1-1]

የዕረቡ ጨዋታዎች

15፡00 – ሚዲአማ (ጋና) ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) [1-3] ኤሲፖንግ ስፖርትስ ስታዲየም

15፡00 – ሳግራዳ ኤስፔራንሳ (አንጎላ) ከ ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) [0-2] ስታዲዮ ሳግራዳ ኤስፔራንሳ

15፡00 – ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን) ከ ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ) [0-2] ስታደ አውገስቲን ሞንዳን

19፡00 – ምስር አል ማቃሳ (ግብፅ) ከ አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) [0-0] ፋዩም ስታዲየም

20፡00 – ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ) ከ ኤል ሜሪክ (ሱዳን) [0-1] ግራንድ ስታደ ማራካሽ

20፡30 – ፋት ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ) ከ ስታደ ማሊያን (ማሊ) [0-0] ኮምፕሌክስ ስፖርቲፍ ሞላይ አል ሃሰን

 

የፎቶ ምንጮች : CAF, AFP

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *