ፕሪሚየር ሊግ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቻምፒዮንነቱ ሲገሰግስ ሀዲያ ሆሳዕና ወደ ከፍተኛ ሊጉ አንድ እግሩን አስገብቷል

-ሁሉም ጨዋታዎች በመሸናነፍ ተጠናቀዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ሲጠናቀቁ ሁሉም ጨዋታዎች በመሸናነፍ ተጠናቀዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቻምፒዮንነት ግስጋሴውን ያሳመረበትን ውጤት ሲያስመዘግብ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ንግድ ባንክ እና ወላይታ ድቻም ድ ቀንቷቸዋል፡፡ የሀዲያ ሆሳዕና ወደ ከፍተኛ ሊግ ጉዞም ፍጥነቱን ጨምሮ ቀጥሏል፡፡

PicsArt_1463597032510

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደደቢትን በመርታት ወደ ዋንጫው ተጠግቷል
 
በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደደቢትን 3-0 በማሸነፍ ወደ ቻምፒዮንነት የሚያደርገውን ጉዞ አሳምሯል፡፡

በ33 ኛው ደቂቃ የዕለቱ ዳኛ ብሩክ የማነብርሃን የሰጡትን አጨቃጫቂ የፍፁም ቅጣት ምት አዳነ ግርማ መትቶ ብርሃነ ቢያድነውም ራምኬል ሎክ በፍጥነት ደርሶ ወደ ጎልነት ቀይሮታል፡፡ ከዚህ ጎል መቆጠር በኋላ በዕለቱ ከሚጥለው ዝናብ ጋር ተደምሮ ጨዋታው ሀይል ወደተቀላቀለበት እንቅስቃሴ ተለውጧል፡፡
ከእረፍት መልስ 72ኛ ደቂቃ ሳላዲን ሰኢድ ሁለት ተከላካዮችን አልፎ  የሰጠውን ኳስ ምንተስኖት አዳነ ተንሸራቶ ወደ ጎልነት ሲቀይረው በ88ኛው ደቂቃ ላይ በዕለቱ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሳላዲን ሰኢድ ያሻገረውን ኳስ አዳነ ግርማ አስቆጥሮ ፈረሰኞቹ ለዋንጫ የሚያደርጉትን ጉዞ አሳምሮላቸዋል፡፡ በአንጻሩ ደደቢት በ2ኛው ዙር ማግኘት ከሚገባው 21 ነጥብ 4 ብቻ በመሰብሰብ ከቻምፒዮንነት ፉክክሩ ለመራቅ ተገዷል፡፡

PicsArt_1463597190570

ባንክ ድሬዳዋን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 5 ከፍ አድርጓል
 
የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ከ ድሬደዋ ከተማ ባገናኘው የ11:30 የአዲስ አበባ ስቴዲዮም ጨዋታ ባንክ 3-0 አሸንፏል፡፡ ገና ጨዋታው በጀመረ በ3ኛው ደቂቃ ፍቅርየሱስ ተ/ብርሃን ንግድ ባንኮችን ቀዳሚ ሲያደርግ ከእረፍት መልስ በ54ኛው ደቂቃ ከሲሳይ ቶሊ የደረሰውን ጣጣውን የጨረሰ ኳስ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን በድጋሚ አስቆጥሯል፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ የ1ደቂቃ እድሜ ሲቀረው  አለቀ ሲባል ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን ግብ ጠባቂውን ጭምር አልፎ ግሩም ጎል በማስቆጠር ሐት-ትሪክ ሰርቷል፡፡

PicsArt_1463597114825

ኢትዮጵያ ቡና የሁለተኛ ዙር ድንቅ አቋሙን ቀጥሎበታል
 
10፡00 ላይ በአበበ ቢቂላ ስታድየም አርባምንጭ ከተማን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና 1-0 በማሸነፍ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ተመልሷል፡፡ ጨዋታው ከመጀመረ አስቀድሞ ተመልካቾች በተገቢው ሁኔታ ባለመስተናገዳቸው ትርምሶች የነበሩ ሲሆን ትኬቶች የተሸጡት እንዲሁም መግቢያ በሮች የተከፈቱት እጅግ ዘግይተው ነው፡፡

በጨዋታው የእንቅስቃሴ የበላይነት የነበራቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች ግብ ለማስቆጠር  የጨዋታው። 2/3ኛ ክፍለ ጊዜ እስኪገባደድ መጠበቅ ግድ ሆኖባቸው ነበር፡፡ በ75ኛው ደቂቃ አማኑኤል ዮሃንስ ከመስኡድ የተሻገረለትን ኳስ በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሮ ቡናን ለድል አብቅቷል፡፡

PicsArt_1463597233123

ድቻ ከ5 ተከታታይ የአቻ ውጤት በኋላ ወደ አሸናፊነት ሲመለስ ሀዲያ ሆሳዕና ለመውረድ ተቃርቧል
 
ቦዲቲ ላይ ሀዲያ ሆሳዕናን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ 2-0 በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 4ኛ ከፍ አድርጓል፡፡ የወላይታ ድቻን የድል ግቦች ከመረብ ያሳረፉት መሳይ አንጪሶ እና በዛብህ መለዮ ናቸው፡፡ በውድድር ዘመኑ ወላታ ድቻን ብቻ ያሸነፈው ሀዲያ ሆሳዕና 7 ነጥብ ይዞ ከፊቱ ከሚገኙት ክለቦች በ15 ነጥቦች ርቆ። ተቀምጧል፡፡ 6 ጨዋታዎች ብቻ በቀሩት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዲያ ሆሳዕና በሊጉ ለመቆየት ያለው ተስፋ እጅግ የጠበበ ነው፡፡
 
ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ፣ ሀሪሰን ሄሱ ፣ ወንድወሰን አሸናፊ ፣ የ7ኛ እና 20ኛ ሳምንት አስገራሚ መገጣጠም ፣ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ. . .
 
-ባለፈው እሁድ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አባት ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት ጨዋታ ታውሰዋል፡፡ ተጫዋቾች የአሰልጣኙን ምስል የያዘ ባነር ይዘው ሲገቡ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊትም የህሊና ፀሎት ተደርጎላቸዋል፡፡
 
-የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አማካይ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ድሬዳዋ ከተማ ላ 3 ግቦች በማስቆጠር ሐት-ትሪክ ሰርቷል፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ኤሌክትሪክን ለቆ ባንክን የተቀላቀለው ፍቅረየሱስ ከዳሽን ቢራው ኤዶም ሆሶውሮቪ እና ኢትዮጵያ ቡናው ሳዲቅ ሴቾ በመቀጠል በውድድር ዘመኑ ሀት-ትሪክ የሰራ 3ኛው ተጫዋች ሆኗል፡፡
 
-የወላይታ ድቻው ወንድወሰን አሸናፊ እና የኢትዮጵያ ቡናው ሀሪሰን ሄሱ በሁለተኛው ዙር ምንም ግብ ያላስተናገዱ ግብ ጠባቂዎች ሆነዋል፡፡ ሁለቱ ግብ ጠባቂዎች ለመጨረሻ ጊዜ ግብ ያስተናገዱት ቦዲቲ ላይ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ ቡናን 2-1 ባሸነፈበት የአንደኛው ዙር የመጨረሻ ጨዋታ ነበር፡፡
 
-በ20ኛው ሳምንት የተደረጉ ጨዋታዎች በሙሉ በመሸናነፍ ተጠናቀዋል፡፡ አስገራሚው ነገር ለመጨረሻ ጊዜ ሁሉም ጨዋታ በመሸናነፍ የተጠናቀቀው በ7ኛው ሳምንት ነበር፡፡ (የ7ኛው ሳምንት እና 20ኛው ሳምንት ተጋጣሚዎች ተመሳሳይ ናቸው)

 PicsArt_1463592300572
PicsArt_1463596838575

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *