የቅዱስ ጊዮርጊስ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤውን 1150 የሚጠጉ አባላት በተገኙበት ዛሬ በሚሌንየም አዳራሽ አድርጓል፡፡ የኦዲት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የቦርድ አባላት ምርጫ ተካሂዶም የነበሩት አባላት እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡

በጉባኤው መጀመርያ የክለቡ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብነት ገብረመስቀል የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የክለቡን ያለፈው አመት አፈጻፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በንግግራቸው መጨረሻም ጠቅላላ ጉባኤው ካለፈለጋቸው በክለቡ ሊቀመንበርነታቸው እንደማይቀጥሉ በመግለፅ ወደ መቀመጫቸው ተመልሰዋል፡፡

PicsArt_1465152001383

የክለቡ የፋይናንስ ሪፖርት ደግሞ በውጭ ኦዲተር ከተገለፀ በኋላ ሰፊ የውይይት ሰአት የነበረ ሲሆን በርካታ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በጉባኤተኛው ጭብጨባ ታጅበው ተሰንዝረዋል፡፡ የስታድየም ጉዳይ ፣ ለክለቡ ስለማይመጥኑ የውጭ ተጫዋቾች ፣ ጠቅላላ ጉባኤው በወቅቱ እና በጊዜው አለመጠራቱ ፣ ለዋናው ቡድን የሚሰጠውን ትኩረት ያህል ለሌሎች ቡድኖች አለመሰጠት ፣ ክለቡ ተቋማዊ መሰረት ይኑረው እና የመሳሰሉት ላይ ተሳታፊዎች ሀሳብ እና ጥያቄያቸውን ሰንዝረዋል፡፡ በጥያቄዎቹ ላይም ምላሾች ተሰጥተዋል፡፡

ከውይይት ሰአት በኋላ የቦርድ አባላት ምርጫ የተከናወነ ሲሆን አቶ አብነት ገብረመስቀል እና ሌሎች የቦርድ አባላት እንዲቀጥሉ በጉባኤው አባላት ተወስኗል፡፡ አቶ ዳዊት ውብሸት አቶ ታደሰ ጥላሁንን በመተካት በስራ አመራር ቦርዱ ውስጥ የተካተተ አዲስ ተመራጭ ነው፡፡

PicsArt_1465151786552 PicsArt_1465151946337

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *